Events

Events የቅርብ ጊዜ ሁነቶች

image description
Start Date icon
End Date icon
Location የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

"አስተማሪ ቅጣት የሌላት አገር በምንም አይነት የፀረ-ሙስና ትግሏ ስኬታማ ሊሆን አይችልም።"  ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን 20ኛውን አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን "ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በሕብረት እንታገል!" በሚል መሪ ቃል የማጠቃለያ ስነ-ሥርዓት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል አደራሽ ህዳር 25/2016 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

በማጠቃለያ መድረኩ ላይ የተገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በማቋቋም የፀረ-ሙስና ትግሉን ተቋማዊ አድርጎ ተጨባጭ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል። ከንቲባ አዳነች አክለውም ሙስና አገርን ከውስጥ የሚበላ ነቀዝ ነው ያሉ ሲሆን፣ የአንድን አገር እድገት በእጅጉ የሚጎዳ፣ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዳይኖር የሚያደርግ፣ አገር ገቢዋን በአግባቡ እንዳትሰበስብ የሚያደርግ እና የንግድ ስርዓት በአግባቡ እንዳይከወን የሚያደርግ ለነገ የማይባል እና የሁሉን ርብርብ የሚሻ ጉዳይ ነው ብለዋል።

ሙስናን መፀየፍ ላይ አንደበታችን ለግንዛቤ ስራ፣ እጃችን ለንፅህና፣ ሞራላችንም በፍፁም ልዕልና ሊቆም ይገባል ያሉት ከንቲባ አዳነች የከተማችን አመራር የሙስናን ተግባር ለመከላከል የአሰራር ስርዓትን ማዘመን፣ ግልፅነት በተሞላበት ሂደት መስራትና ተቀናጅቶ መታገልን ቅድሚያ ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ በአፅንኦት ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ስነምግባር ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጀማል ረዲ በበኩላቸው የዘንድሮ 20ኛው የፀረ ሙስና ቀን ስናከብር በከተማ አስተዳደሩ በፀረ ሙስና ትግሉ ያሉ መሻሻሎችን በማስቀጠል እና አመራሩና ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ በማነሳሳት እንደሆነ ተናግረዉ በዚሁ መሠረትም የፀረ ሙስና ትግሉ ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ሙስና ባደጉትም ሆነ ባላደጉት ሀገራት የሰላምና የልማት ፈተና መሆኑን የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡት የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር አሰፋ ቶላ በመድረኩ ላይ አመላክተዋል፡፡ የሙስና መንስዔ የስነ ምግባር ዝቅጠት መሆኑን ያነሱት ም/ኮሚሽነሩ ኮሚሽኑ በቀዳሚነት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በርካታ የስነ ምግባር ግንባታ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም ከስነምግባር ግንባታው ጎን ለጎን የሙስና መከላከል ሥራዎች በመሰራታቸው አበረታች ውጤት መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና ጥሪ የተደረጋለው እንግዶች የተሳተፉ ሲሆን የጋራ ጠላት የሆነውን ሙስና ለመከላከል ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ መስራት  እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡


Related Events

image description
የቅርብ ጊዜ ሁነቶች

  • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
More Details
image description
የቅርብ ጊዜ ሁነቶች

  • አዲስ አበባ ባህልና ቲያትር አዳራሽ
More Details
image description
የቅርብ ጊዜ ሁነቶች

  • በወዳጅነት ፓርክ
More Details
image description
የቅርብ ጊዜ ሁነቶች

  • አደዋ 00 ፓርክ
More Details
image description
የቅርብ ጊዜ ሁነቶች

  • አደዋ 00 ፓርክ
More Details