የመከታተያ ክፍሎች ህግና ደንብን የማስከበር ሚና...

image description
image description
image description
image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

የመከታተያ ክፍሎች ህግና ደንብን የማስከበር ሚናቸውን አጠናክረው ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ።

የመከታተያ ክፍሎች ህግና ደንብን የማስከበር ሚናቸውን አጠናክረው ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ።

***************

ህዳር 02/2019 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች የተቋቋሙበትን ዋና ዓላማ በውል በመረዳት በተቋማት ውስጥ የሕግ እና የደንብ ተፈጻሚነትን የማረጋገጥ ስራቸውን አጠናክረው መስራት እንዳለባቸው የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሀብታሙ ፈይሳ ገልፀዋል።

እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች የተቋቋሙበትን አላማ ተረድተው የተቋማትን አሰራር ስርአት የህግ አከባበርና የደንብ ተፈጻሚነት በቅርበት የማረጋገጥ ከፍተኛ ሀላፊነት አለባቸው ብለዋል።

መከታተያ ክፍሎቹ የስነ-ምግባር ጥሰቶችን የማረም፣ ጥቆማዎችን በንቃት ተቀብሎ ለጠቋሚዎች ተገቢውን ጥበቃ የማድረግ፣ በጥፋተኞች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችን የመከታተል፣ የሀብት ምዝገባ ስራዎችን የማከናወን እንዲሁም አስፈላጊ መረጃዎችንና ሪፖርቶችን በወቅቱ ለኮሚሽኑ የማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው ምክትል ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

የተጣለባቸውን ሀላፊነት በማይወጡ አካላት ላይ ኮሚሽኑ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ኮሚሽነር ሀብታሙ ፈይሳ አሳስበዋል።

 


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments