23ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል በል...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

23ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል በልዩ ልዩ ሁነቶች እንደሚከበር ተገለፀ።

23ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል በልዩ ልዩ ሁነቶች እንደሚከበር ተገለፀ።

************

በአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የ23ኛው ዓለም ዓቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በዓል አከባበር  ማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ የከተማና የክፍለ ከተማ አፈ ጉባኤዎች እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊዎች እንዲሁም ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ አመራሮች እና ባለሙያዎች በተገኙበት ውይይት ተካሄደ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊና የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከድር ማሞ የጋራ ጠላታችን የሆነው ሙስና ሀገርን የሚጎዳና ህዝብ በመንግስት ላይ ያለውን እምነት የሚያሳጣ መሆኑን አንስተው እስካሁን በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ ውጤታማ የሙስና መከላከል ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀዋል።

ይበልጥ  ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አመራሩ በተለየ ትኩረት ንቅናቄውን መምራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

አክለውም በበዓሉ አከባበር ወቅት የሚካሄዱ የንቅናቄ ስራዎች የህዝቡን የፀረ ሙስና ትግል ግንዛቤ በማሳደግ የፀረ ሙስና ትግል እገዛው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አመራሩ በትኩረት ሊመራው እንደሚገባም አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሪት ፋኢዛ መሀመድ ሙስናን መታገል ዓመቱን በሙሉ የሚከወን ተግባር  ቢሆንም እነዚህ የንቅናቄ መድረኮች ትግሉን ለሰፊው የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ ጠቃሚ እንደሆኑ በመግለፅ ፈጥኖ ወደ ስራ መግባት አንደሚያስፈልግሞ ገልፀዋል።

 ሙስና በሀገር ላይ የሚያደርሰውን  አደጋ ለመግታት ሙሰኞች የሚፈጥሩትን የጥቅም ትስስር መበጠስ እንደሚገባ የተናገሩት  የአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ በበዓሉ አከባበር ወቅት የሚከናወኑ የንቅናቄ ስራዎች ለሙስና ትግሉ አቅም በመሆን የሙስና ትግሉን ይበልጥ ለማቀጣጠል ወሳኝ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

 የበዓልሉን አከባበር የተመለከተ ማስፈፀሚያ ዕቅድ እና የትኩረት አቅጣጫ በም/ኮሚሽነር መቅደስ ተስፋዬ ቀርቧል።

በመድረኩ ዓለም ዓቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ  በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ23ኛ ጊዜ "ስውር ትስስሮችን በማጋለግጥ፤  የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ!" በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተነስቷል።

የውይይቱ ተሳታፊ ኃላፊዎችም በበዓሉ አከባበር ሂደት የሚከናወኑ የተለያዩ ሁነቶችን በተሳካ ሁኔታ እንዲፈፀሙ ተቋማትንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩም ገልፀዋል።

ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments