ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳደግ የሙስና ትግሉን ው...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳደግ የሙስና ትግሉን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ፡፡

ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳደግ  የሙስና ትግሉን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ፡፡

****************

የአዲስ አበባ ከተማ ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ ሙስና ልማትንና መልካም አስተዳደርን የሚጎዳ በመሆኑ፣ ተፅዕኖውን ለመግታት የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። እንደ ሀገር ሁላችንንም ጎጂ በመሆኑ የአንድ ተቋም ብቻ ተግባር ሊሆን እንደማይገባም አንስተዋል።

እስካሁን በቅንጅት በተሰሩ የስነ ምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል  ስራዎች የሙስና ትግሉን ውጤታማ ማድረግ እንደተቻለ ኮሚሽነሩ  አብራርተዋል።

አክለውም በቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚኖረውን ትስስር ይበልጥ በማጠናከር የትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ስራ፣ የተቋማት አሰራር ስርዓት ለሙስና ተጋላጭ እንዳይሆን የማድረግ እና ሙስናን በማስረጃና በመረጃ በመታገል ተጠያቂነትን የማስፈን ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስገንዝበዋል።  

ባለድርሻ አካላቱ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በመወጣት የሙስና ወንጀልን በጋራ ለመከላከል በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ይህ አይነቱ ቅንጅታዊ ስራ በሙስና ትግሉ ላይ መነሳሳትን የሚፈጥርና የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የሚያፋጥን መሆኑም ተመላክቷል።

የኮሚሽኑን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ ከፍተኛ ሚና ካላቸው ባለድርሻ አካላት ጋር  ስምምነት ሰነዱን በመፈራረው የበጀት ዓመቱ  ቅንጅታዊ ስራ ኮሚሽኑ በይፋ አስጀምሯል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments