ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- Events info news    0

ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር እየሰራ ያሉትን ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ።

ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር እየሰራ ያሉትን ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን የስራ ምልከታ አድርገዋል፡፡

ከኢንስቲትዩቱ ጋር ከዚህ በፊትም በተለያዩ ስራዎች በቅንጅት እየተሰራ ሲሆን የአሰራር ግልጽነትን በማሳደግ፤ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ በማድረግ ሙስናን በመከላከልና ተጠያቂነትን በማስፈን ረገድ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የኤ አይ ቴክኖሎጅ ውስብስብ የሆኑ የሙስና ወንጀሎችን በቀላሉ ለማጋለጥ እና ዜጎች በምስጢር ጥቆማ እንዲሰጡ ከማስቻል ባሻገር በቴክኖሎጂ የታነጸ ታማኝ ትውልድ ማፍራት እንድሁም ፍትሐዊነትንና እኩልነትን ማስተማር እንዲለማመድ የሚያግዝ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በምልከታው የኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎች የታዩ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመሩ የዲጂታላይዜሽን ጉዞ እውን ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል።

የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች በበኩላቸው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በትውልድ ስነ ምግባር ግንባታና ሙስናን ለመከላከል እንደ ኮሚሽን በሚደረገው ጥረት ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

በመጨረሻም እንደ ኮሚሽን የሚሰጡ አገልግሎቶች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ በማዘመን ቀልጣፋና ግልጽነት ያለው አሰራር ለመዘርጋት የሚያስችል ተግባሮችን ለመፈጸም ቅንጅታዊ አሰራሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments