የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5 ዓመት ማጠቃለያ የዕውቅና እና የምስጋና መድረክ አካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5 ዓመት ማጠቃለያ የዕውቅና እና የምስጋና መድረክ አካሄደ።
*************
በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ባለፉት ለውጥ ዓመታት በቋሚ ኮሚቴው ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር አማካኝነት አስፈጻሚ አካላት በህግ የተሰጣቸውን ኃላፊነትና ተግባራት ቆጥረው እንዲፈጽሙ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።
በተለይም የተደራጀ ሌብነትና ሙስና እንዳይስፋፋ በማድረግ፣ የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነት እንዲያድግ እና ሕዝቡ በመንግስት ላይ ያለው አመኔታ እንዲጠናከር ከሠሩ ተቋማት መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጎላ ሚና እንደነበረው ተመላክቷል።
ኮሚሽኑ ህዝብን ማዕከል ባደረገ አሰራርና በቁርጠኝነት ያከናወናቸው የሥራ አፈጻጸሞች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸው ተነግሮ ምስጋና ቀርቦለታል።
በመጨረሻም ለተቋሙ ባለፉት ዓመታት ለነበረው ጠንካራ አፈጻጸም እና የፀረ-ሙስና ትግል ስራዎች የዕውቅና እና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments