ኮሚሽኑ 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ...

image description
image description
image description
image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

ኮሚሽኑ 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ፤

ኮሚሽኑ 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ፤

የፌደራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተመሠረተበትን 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ መርሃ-ግብር አካሄደ።

ኮሚሽኑ ባለፉት የሩብ ክፍለ-ዘመን ጉዞው በሀገሪቱ የሥነምግባር እሴቶችን በመገንባት፣ የሙስና ስጋቶችን በቅድመ-መከላከል ስራዎች በማስወገድ እንዲሁም የህግ ማስከበር ተግባራትን በስፋት በማከናወን ረገድ በርካታ አዎንታዊ ውጤቶችን ማስመዝገቡ በመድረኩ ተገልጿል።

በመድረኩ ኮሚሽኑ በ25 ዓመቱ የፀረ-ሙስና ትግሉ ትናንት፣ ዛሬ እና ነገን ላይ ትኩረት ያደረጉ ዶክመተሪ ፕሮግራም እና የመወያያ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።

በመርሃ-ግብሩ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የሥነምግባር ግንባታ፣ የሙስና ቅድመ መከላከል እና የሙስና ወንጀል  የህግ ማስከበር ዋና ዋና ተግባራት፤ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ይደረጋል።

በዚሁ ታሪካዊ የማጠቃለያ መርሃ-ግብር ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶን ጨምሮ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና አባላት፣ የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽነሮችና የቀድሞ ኮሚሽነሮች፣  እንዲሁም የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች መሳተፋቸውን ኮሚሽኑ በማህበራዊ ገፁ አጋርቷል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments