በስነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል በ2018...

image description
image description
image description
image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

በስነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት መመዝገቡ ተገለፀ፡፡

በስነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት መመዝገቡ ተገለፀ፡፡

**************

የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2018 በጀት አመት በትውልድ ስነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ተግባራት ላይ በተከናወኑ ስራዎች የላቀ ውጤት መመዝገቡን አስታወቀ።

የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ እና ስኬታማ ለማድረግ ህብረተሰቡን ባማከለ መልኩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተለያየ መድረክ ማሳተፍ እንደተቻለ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጀማል ረዲ ገልጸዋል።

በበጀት አመቱ በደረጃው ያሉ የመከታተያ ክፍሎችን በተለያዩ ጊዜያት ድጋፍና ክትትል በማድረግ እንድሁም ተገቢውን ምዘና በማካሄድግ የማብቃት ስራ ለመስራት ጥረት መደረጉን የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ሃብታሙ ፈይሳ ገልፀው የሃብት ምዝገባ እና ትክክለኛነትን የማረጋገጥ ተግባር ቴክኖሎጅን በመጠቀም ለመስራት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ም/ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

የማህበረሰቡን ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሳደግ ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥ ሃሎችን ለማበራከት ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ የኮሚሽኑ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፈቱ ሰማን ገልጸዉ የሰራተኛውን የሙያና የተቋማዊ አቅም ለማሳደግም የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ረገድ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ውስጥ ከ 13 ተቋማት ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራርሞ ወደ ስራ መገባቱን፣ በተለያዩ መድረኮች ለ1.6 ሚሊዬን የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ መፈጠሩን፣ ለ204,060 አመራሮች፣ ለመንግስት ሰራተኞችና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ስልጠና መሰጠቱን፣ የ57,812 አመራርና ባለሙዎች ሃብት መመዝገቡን፣ 16 የሙስና ተጋላጭነት ጥናት መሰራቱን፣ በመደበኛና በአስቸኳይ ሙስና መከላከል በገንዘብ 706,630,383.76 ብር ማዳን መቻሉን፣ በብልሹ አሰራርና በስነ ምግባር ችግር ውስጥ የተገኙ 1917 አመራርና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን እና 1822 የሙስና ወንጀል ጥቆማ ቀርቦ መተንተኑን በኮሚሽን ሪፖርት ተመላክቷል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments