የአዲስ አበባና የፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች በጋራ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።
የአዲስ አበባና የፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች በጋራ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አቃቂ ብረታ ብረት ፋብሪካ አካባቢ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሂደዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ እንደገለጹት ሀገራችን ለ8ኛ ጊዜ እያካሄደች በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የዘንድሮው የትኩረት አቅጣጫ ለምግብነት የሚያገለግሉ የችግኝ ዝርያዎችን በመምረጥ መትከል፣ ከጽደቃቸው ባለፈም ተንከባክቦ ለውጤት ማብቃት ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል።
የፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው የመርሃ-ግብሩ መካሄድ የሰላም፣ የእድገትና የህብረ-ብሄራዊ ተስፋን በማለምለም «ችግኝ በመትከል ችግርን መንቀል» የሚለውን ታላቅ ዓላማ ያነገበ መሆኑን አስረድተዋል።
በተመሳሳይ ኮሚሽነር እሸቴ አስፋው ሀገራችን በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል የላቀ ድልና ተስፋ ማስመዝገቧን ገልጸዋል። አያይዘውም በኮሚሽኑ ደረጃ 14 ሺህ ችግኞች መተከላቸውን በመጥቀስ፣ ለዚህ አገራዊና ተቋማዊ ስራ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አካባቢ በመገኘት ከ4 ሺህ በላይ ችግኞችን መትከላቸው ተገልጿል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments