"ችግኞችን እንተክላለን፤ ትውልድን በስነ ምግባር...

image description
image description
image description
image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

"ችግኞችን እንተክላለን፤ ትውልድን በስነ ምግባር እንገነባለን"- ኮሚሽነር ጀማል ረዲ

"ችግኞችን እንተክላለን፤ ትውልድን በስነ ምግባር እንገነባለን"-

ኮሚሽነር ጀማል ረዲ

 

የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች አመራርና ሰራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሀሳብ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጀማል ረዲ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ችግኝ ከመትከል ባለፈ ለኑሮ ተስማሚ የሆነ የአየር ንብረት በመፍጠርና አረንጓዴ ከተማን እውን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም "ችግኞችን እንተክላለን፤ ትውልድን በሥነ-ምግባር እንገነባለን" በማለት የሥነ-ምህዳር ጥበቃው ከትውልድ ግንባታ ሥራ ጋር ተቀናጅቶ ሊሄድ እንደሚገባ አሳስበዋል። በተጨማሪም ዛሬ የተተከሉትን ችግኞች ከመደበኛ ተቋማዊ ሥራዎች ጎን ለጎን ቀጣይነት ባለው መልኩ እንክብካቤ የሚደረግበት ሥርዓት እንደሚዘረጋ አመላክተዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የተሳተፉት የቦሌ ክፍለ ከተማ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ለማ በበኩላቸው፤ ኮሚሽኑ በተለያዩ አካላት ሊመዘበር የነበረን የሕዝብና የመንግሥት ሀብት በማስከበርና በመከላከል ረገድ አዲስ አበባ ከተማ ላስመዘገበችው ሁለንተናዊ ዕድገት ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

አረንጓዴ አሻራን እውን በማድረግ ረገድም ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን በመንከባከብ እንዲጸድቁ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የአካባቢያችንን ሥነ-ምህዳር ለመጠበቅ እንዲሁም የወንዝ ዳርቻዎችን ከብክለትና ከመሸርሸር ለመታደግ ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት ይኖርብናል ሲሉ አቶ ክፍሌ ለማ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments