ሀገር የምትገነባው መልካም ስነ-ምግባር ባላቸው ዜጎች ነው
"ሀገር የምትገነባው መልካም ስነ-ምግባር ባላቸው ዜጎች ነው" - ኮሚሽነር ጀማል ረዲ
******************
የአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሸን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ አመቱን በሙሉ ሲከናወን የቆየው የትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ስራዎች የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎችን ብቁ፣ በግብረገብ የታነጹ እና ሀገር ወዳድ እንዲሆኑ ለማድረግ እና ሙስና የልማትና መልካም አስተዳደር ስጋት የማይሆንባት ከተማን ለመፍጠር አጋዥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ኮሚሽነሩ አክለዉም እነዚህ በስነምግባር አርዓያ በመሆን የተመረጡ ተማሪዎች የተሰጣቸውን አደራ በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አመላክተዋል።
እነዚህ ተማሪዎች ያሳዩትን መልካም አርአያነት በጽናት አስጠብቀው በመቀጠል፣ ለሌሎች አቻዎቻቸውና ተማሪዎች ተምሳሌት መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
የነገ ሀገር ተረካቢዎችን በስፋት ለመፍጠር ኮሚሽኑ ከከተማው ትምህርት ቢሮ ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት ኮሚሽነር ጀማል ሀገር የምትገነባው መልካም ስነ-ምግባር ባላቸው ዜጎች በመሆኑ በትምህርት ቤቶች በሚገኙ ክበባት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ዜጎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ብቁ ከመሆናቸው ባሻገር፣ በስነ-ምግባር የታነጹና ለሙያቸው ታማኝ መሆን እንደሚገባቸውም በንግግራቸው አጽንኦት ሰጥተውበታል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments