



ደሜን በመለገስ ወገኔን እታደጋለሁ!
ደሜን በመለገስ ወገኔን እታደጋለሁ!
የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች የደም ልገሳ መርሀ ግብር አካሄደዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች ''ደሜን በመለገስ ወገኔን እታደጋለሁ! ''በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች አንዱ የሆነውን የደም ልገሳ መርሀ ግብር አካሄደዋል፡፡
የኮሚሽኑ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፈቱ ሰማን በደም ልገሳው ወቅት ኮሚሽኑ በአዋጅ ተቋቁም ወደ ስራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ከትውልድ ስነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ጎን ለጎን በበጎ አድራጎትና በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ ፡፡
የኮሚሽኑ አመራና ባለሙያዎች ከክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች መካከል አንዱ የሆነውን የደም ልገሳ መርሀ ግብር ላይ ተሳተፊ መሆናቸው በደም እጥረት ህይወታቸውን ለሚያጡ ወገኖች ቀድሞ ለመድረስ የሚያስች ተግባር እንደሆነም ገልፀዋል፡፡
ኮሚሽኑ ከክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት ባለፈ በመደበኛነት 4 ህፃናትን በማሳደግ፣ በዓላትን ታሳቢ ያደረጉ አቅም ለሌላቸው ዜጎች የማዕድ ማጋራትና በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ላይም የጓላ ተሳትፎ እንዳለው አቶ ፈቱ ጠቁመዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments