



"ትምህርት ቤቶች በስነ ምግባር የታነፀ ትውልድ በማፍራት ረገድ የማይተካ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል" ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ከአስራ አንዱም ክ/ከተማ ለተውጣጡ መልካም ስነ ምግባር ላላቸው ተማሪዎች "ስነ ምግባር ያሸልማል" በሚል የእውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር አካሄደ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ትምህርት ቤቶች በስነ ምግባር የታነፀ ትውልድ በማፍራት ረገድ የማይተካ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
ት/ቤቶች እውቀትና ክህሎትን ከማስጨበጥ ባሻገር በስነ ምግባራቸው አርአያ የሆኑ ተማሪዎችን እንድያበራክቱ በማድረግ ረገድ ኮሚሽኑ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ዶ/ር ዘላለም ገልፀዋል።
የኮሚሽኑ ኮሚነር ጀማል ረዲ የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች ከትምህርታቸዉ ጎን ለጎን የሙስናን አስከፊነት እና አስፀያፊነት ተገንዝበዉ በመልካም ስነ ምግባር ታንፀዉ እንዲያድጉ ኮሚሽኑ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ አየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ተማሪዎችን በመልካም ስነ ምግባር በማነፅ ሂደት ውስጥ የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ክበባት አስተዋፆኦ የጎላ መሆኑን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም የተሻለ አፈፃፀምና ልምዳቸውን ላካፈሉ ለስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ክበባት፣ በሰነ ምግባራቸው ውጤታማ ተማሪዎችን ላፈሩ ት/ቤቶችና ከአስራ አንዱም ክ/ከተማ ለተውጣጡ መልካም ስነ ምግባር ላላቸው ተማሪዎች እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
"ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments