ሀገራዊ መልካም እሴቶችን በማጠናከር በትውልድ ስ...

image description
image description
image description
image description
- Events info news    0

ሀገራዊ መልካም እሴቶችን በማጠናከር በትውልድ ስነ ምግባር ግንባታ ላይ በቀዳሚነት ሊሰራ ይገባል።" የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ

ኮሚሽኑ የ2017 በጀት አመት ከተማ አቀፍ የተማሪዎች የስነ ምግባር ጥያቄና መልስ ውድድር ከመንግስትና ከግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ ተማሪዎች መካከል አካሄደ።

በመር-ሃግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ የኮሚሽኑ አመራሮች፤ የአዲስ አበባ ከተማ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ መሪዎች፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፤ ወላጆች እና ተማሪዎች ታድመዋል።

በመርሃ ግብሩ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ሀገርን ለዘርፈ ብዙ ችግር የሚያጋልጠውን የስነ ምግባር ችግር ለመቅረፍና ሙስናን ለመከላከል በትውልዱ ላይ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል። ሀገራዊ መልካም እሴቶችን በማጠናከር በትውልድ ስነ ምግባር ግንባታ ላይ የሚመለከታቸው ተቋማት በቀዳሚነት ሊሰሩ ይገባል ሲሉ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ ከትምህርት ተቋማት ጋር በመቀናጀት በትውልድ ስነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል በርካታ ስራዎች መስራቱን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጀማል ረዲ ገልፀዋል። የጥያቄና መልስ ውድድሩ አላማ ተማሪዎች በትምህርታቸውና በስነ ምግባራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ፤ ሙስና አለም አቀፍ የልማት ፀር መሆኑን እንዲረዱ እና ነገ የሚረከቧትን ሀገር ህግና ስርአት ተረድተው የሙስና ትግሉ ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑን ኮሚሽነር ጀማል ተናግረዋል።

በውድድሩ 1ኛ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ሱመያ ትምህርት ቤት ተማሪ ዳንያ ሁሴን፣ 2ኛ ከአራዳ ክፍለ ከተማ አቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤት ተማሪ ሴትና ፍፁም እና 3ኛ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ኡላዱላ ትምህርት ቤት ተማሪ ኤልቤቴል አበበ የሞባይል ስልክና ሰርተፊኬት እንዲሁም ተማሪዎችን ያሳተፉ ትምህርትቤቶችና ተሳታፊ ተማሪዎች የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቷል።

"ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments