

ወጣቶችን በስነ ምግባር በማነፅ እምነት የሚጣልባቸውና ሀገር እንዲረከቡ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ለወጣቶች ማህበር አመራሮችና አባላት በወጣቶች ሊተገበሩ በሚገቡ የገብረ ገብ እሴቶችና ፋይዳው በሚል ስልጠና ሰጠ።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር መቅደስ ተስፋዬ በየካ ክፍለ ከተማ ተገኝተው ስልጠናው በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት ኮሚሽኑ በትውልድ ስነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ከወጣት አደረጃጀቶች ጋር መሥራት ውጤታማ ያደርገናል ብለዋል፡፡
ወጣቶች የማህበረሰቡ ከፍተኛ ቁጥር የያዙ በመሆናቸው ወጣቱን በስነ ምግባር በማነፅ እምነት የሚጣልባቸውና የሀገርን ኃላፊነት የሚረከቡ ብቁ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ወጣቱ ከሙስናና ብልሹ አሰራር ራሱን በመጠብቅ ሙስና ተፈፅሞ ሲገኝም በመታገል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ስልጠናው በ11ዱም ክፍለ ከተሞች በተመሳሳይ ሰዓት የተሰጠ ሲሆን ከ1700 መቶ በላይ ወጣቶች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡
"ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments