

ሴቶች ራሳቸውን በስነ ምግባር በማነፅና ሙስናን የሚፀየፉ በመሆን ግንባር ቀደም ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ለሴቶች ማህበር አመራሮችና አባላት በትውልድ ስነ ምግባር ግንባታ ላይ የሴቶች ሚና በሚል ስልጠና ሰጠ።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር መቅደስ ተስፋዬ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ስልጠናው በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት የከተማችን ሴቶች ራሳቸውን በስነ ምግባር በማነፅ ሙስናን የሚፀየፍ መሆን መቻል አለባቸው ብለዋል፡፡
የሀገር ግንባታ ስር መሰረቱ በስነ ምግባር የተገነባ ትውልድ መፍጠር ያሉት ምክትል ኮሚሽነሯ በትውልድ ስነ ምግባር ግንባታ ደግሞ ከሴቶች ቀድሞ ሊመጣ የሚችል አካል የለም ብለዋል። ሴቶች ይህንን ሚናቸውንም ተረድተው በትውልድ ስነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራው ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
ስልጠናው በ11ዱም ክፍለ ከተሞች በተመሳሳይ ሰዓት የተሰጠ ሲሆን 1760 ተሳታፊ በስልጠናው መሳተፋቸው ታውቋል፡፡
"ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments