የትራፊክ ፖሊሶች በስነ ምግባር አርአያ በመሆን...

image description
image description
image description
image description
image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

የትራፊክ ፖሊሶች በስነ ምግባር አርአያ በመሆን ስራዎቻቸውን ማከናወን እንደሚገባቸው ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ–ሙስና ኮሚሽን ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትራፊክ ቁጥጥር ዲቪዥን ጋር በመተባበር በሙያ ስነ ምግባር ሙስናን መከላከል ላይ ስልጠና ሰጠ።

በስልጠናው ወቅት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር መቅደስ ተስፋዬ የስራ ላይ ስነ ምግባር ስልጠና ህግ ለሚያስከበር ተቋማት አመራርና ሠራተኞች ወሳኝ መሆኑን ገልፀው የስነ ምግባር ስራችንን ለማከናወን መሰረታዊ ጉዳይ ነው። አያይዘውም የትራፊክ ፖሊስ አባላት በስነ ምግባር አርአያ በመሆን ስራዎቻቸውን ማከናወን እንደሚገባ ገልፀዋል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትራፊክ ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ያደታ ሚደቅሳ በክፍለ ከተማችን ከኮሚሽኑ ጋር በመተባበር ስልጠና ሲሰጥ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ ቀደም በወሰድነው ስልጠና በ2016 ያስመዘገብነው ውጤት ምስክር ነው ብለዋል። ክፍለ ከተማው በርካታ ባለስልጣናት፣ ዲፕሎማቶችና አለም አቀፍ ተቋማት መገኛ በመሆኑ ስራችንን በዕውቀትና በስነ ምግባር መስራት ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ስልጠናውን የሰጡት የስልጠና ክፍል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀንበሩ ኢርኮ በበኩላቸው የትራፊክ ፖሊስ አባላት ስራቸውን በሙያ ስነ ምግባር ለማከናወን ስልጠናው ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

የትራፊክ ፖሊስ ስራ አካላዊም ሆነ አእምሮአዊ ብቃት የሚያስፈልገው በመሆኑ አባላቱ ራሳቸውን እያበቁ መሄድ ተገቢ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ የሚመጡ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከሙያ ስነ ምግባር ጋር በማጣጣም ስራቸውን በሚፈለገው ልክ መስራት እንደሚያስፈልግ በሰነድ አብራርተዋል።

“ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments