"ወጣቶች የነገ ተስፋችሁና ህልማችሁ እንዳይሰረቅ...

image description
image description
image description
image description
image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

"ወጣቶች የነገ ተስፋችሁና ህልማችሁ እንዳይሰረቅ ሙስናን መታገል አለባችሁ"። ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

በዓለም ለ21ኛ ግዛት በሀገራችን ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው እልም እቅፍ የፀረ ሙስና ቀን ከተማ አቀፍ የማጠናቀቂያ ስነ ስርዓት በአድዋ መታሰቢያ አዳራሽ በድምቀት ተካሄደ፡፡

 

በማጠናቀቂያ ስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በፀረ ሙስና ትግሉ ላይ በተደረጉ ጥረቶች በርካታ ውጤቶች እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል።

የፀረ ሙስና ትግሉ የሚጀምረው ማህበረሰቡ ስለሙስና ያለውን አመለካከት በመቀየርና ግንዛቤ በማሳደግ ነው ያሉት ከንቲባዋ የግንዛቤ ፈጠራና የስብዕና ቀረፃ ስራው የሚጀምረው ከቤተሰብ ሲሆን የሃይማኖት ተቋማትና ትምህርት ቤቶችም የማይተካ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል።

 

አክለውም "ወጣቶች የነገ ተስፋችሁና ህልማችሁ እንዳይሰረቅ ሙስናን መታገል አለባችሁ" ያሉ ሲሆን ሁሉም ማህበረሰብ በተቀመጠለት የትግል አቅጣጫ ውስጥ ገብተው እንዲታገሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ በበኩላቸው የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የፀረ ሙስና ቀን በየዓመቱ በተለያዩ መሪ ቃሎች እንደሚከበር ገልፀው የዘንድሮው "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ ሙስና ትግል የነገ ስብዕና ይገነባል" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል ብለዋል። ሙስና በማህበረሰቡ በተለይም ደግሞ በወጣቶች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ ወጣቶች ህልማቸውን እንዳይኖሩ የሚያደርግ በመሆኑ በጋራ ልንታገለው ይገባል ብለዋል።

 

በማጠናቀቂያ ስነ ስርዓቱ ላይ 21ኛውን አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በከተማ አቀፍ ደረጃ በድምቀት እንዲከበር አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማት የዕውቅናና የምስጋና ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

“ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments