በመልካም ስነ-ምግባራቸው አርአያ ለሆኑ ተማሪዎች...

image description
- Events ሰሞነኛ ዜናዎች    0

በመልካም ስነ-ምግባራቸው አርአያ ለሆኑ ተማሪዎች ዕውቅና ተሰጠ።

በመልካም ስነ-ምግባራቸው አርአያ ለሆኑ ተማሪዎች ዕውቅና ተሰጠ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን  "ስነ ምግባር ያሸልማል!" በሚል መርሃ ግብር የዕውቅናና የሽልማት  ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል።

በከተማዋ በሚገኙ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከት/ት ውጤታቸው ባሻገር መልካም ስነ ምግባር ያላቸውንና ለሌሎች ተማሪዎች አርአያ ለሆኑ ተማሪዎችን ዕውቅናና ሽልማት ተበርክቷል።

መልካም ስነ ምግባር ላላቸው ተማሪዎች ዕውቅና መስጠት ለሌሎች ተማሪዎች መነሳሳትን የሚፈጥር ከመሆኑ በላይ ሀገር የሚረከብ መልካም ስብዕና ያለው ትውልድ ለመፍጠር ሚናው ከፍተኛ ነው።

ሀገር የሚታነፀው መልካም ስነ ምግባር ባላቸው ዜጎች በመሆኑ የነገ ሀገር ተረካቢዎችን ለመፍጠር ኮሚሽኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከሚገኙ ት/ቤቶችና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በመልካም ስነ ምግባራቸውና በአርአያነታቸው የተመረጡ 12 ተማሪዎች ዕውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments